በ10:30 በእለቱ ተጠባቂ ጨዋታ አዳማ ከተማ ከ ጊዲኦ ዲላ ተገናኝተው አዳማ ከተማ 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ተመጣጣኝ የሆነ እና እልህ አስጨራሽ የመሸናነፍ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ
የተቆጠረ ጎል አዳማን ለድል አብቅቷል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ዲላዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ከፍተኛ ተጋድሎ
ቢያደርጉም ጥረታቸው ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል፡፡
በግማሽ ፍጻሜው አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡